15:31

12:32

ትናንት በእስራኤል በተካሄደው 21ኛው ብሄራዊ የክነሴት (ፓርላማ) ምርጫ ውጤት የሊኩድ ፓርቲና የካሆል ላባን ፓርቲ እያንዳንዳቸው 35 መቀመጫ ወንበር ያገኙ ሲሆን ፤ የግራ ዘመም ርዮት የሚከተለው የሰራተኞች ፓርቲ ባሳለፈው ታሪክ ከባድ  ሽንፈት አጋጥሞታል። ሌሎች የግራ ዘመም ፓርቲወችም የሚጠበቀውን ያህል ወንበር አላገኙም።

እስካሁን 97 እጁ የመራጭ ድምጽ የተቆጠረ ቢሆንም ፤ የወታደሮችና በውጭ አገራት የሚያገለግሉ ዲፕሎማቶች ድምጽ ቆጠራ እንደቀጠለ ነው የመጨረሻ ቆጠራው ሲጠናቀቅ እስካሁን የመለኪያ መስፈርቱን ያላለፉ ፓርቲወች ለምሳሌ ናፍታሊ ቤኔትና አየሌት ሸኬድ የሚመሩት ያሚን ሃሃዳሽ የተሰኘው ፓርቲ ሊያልፍ ይችላል የሚል ግምት አለ።

አሁን ባለው ውጤት መሰረት  የሊኩድ ፓርቲ መሪ ቢንያሚን ናታንያሆ የቀኝ ዘመም ፓርቲወችን በማጣመር አዲስ ጥምር መንግስት የማዋቀር እድል እንዳላቸው ተገልጿል።

የቀድሞው ኢታማጆር ሹም የሚመሩት  የካሆል ላባን ፓርቲ የመንግስት ተቃዋሚ ሆኖ ይቀጥላል የሚል ግምት ሲኖር ፤ በዚህ ፓርቲ ስር የተወዳደሩ ሁለት ከኢትዮጵያ  ቤተ እስራኤል አብራክ የወጡት ፕኒና ታምኖና ጋዲ ይባርከን ተመርጠዋል።

23፡15 

ጣቢያዎች ያቀረቡት ናሙና ውጤት፤

የ21ኛው የክኔሴት ምርጫ ናሙና ውጤት፥
ዛሬ ጥዋት 7፡00 ስዓት የተጀመረው 21ኛው የእስራኤል ክኔሴት(ፓርላማ) ምርጫ ከምሽቱ 22፡00 ተጠናቀቀ። የምርጫው ናሙና የሚከተለው ነው።

በእስራኤል ሶስት አንጋፋ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ማለትም ካአን 11ኛው፣ 12ኛውና 13ኛው የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚለተለውን ግምገማ አቅርበዋል።

11ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ

ካሆል ላባን 11ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 37 ፣ 12ኛው ቴሌቪን ጣቢያ 37 ፣ 13ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 36

ሊኩድ 11ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 36 ፣ 12ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 33፣ 13ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 36

ያሃዱት ሃቶራ 11ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 7፣ 12ኛው 7፣ 13ኛው 7

ሻስ 11ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 7፣ 12ኛው ቴሌቪዥን ጣቢያ 6፣ 13ኛው 7 ይመስላል፡፡ የሌሎች ፓርቲዎች ናሙና ውጤቶችም አሉ፡፡ የማዕከላዊ አስመራጭ ኮሚቴ ትክክለኛው ውጤት ከነገ ጀምሮ ይፋ ያደርጋል፡፡

20፡00 

እስከ ምሽቱ 18፡00 የነበረው የመራጮች ድምጽ 52፡% እንደነበር የተለያዩ ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡   

18፡06 

በመላው እስራኤል ዛሬ እየተካሄደ ባለው ምርጫ እስከ ቀኑ አራት  ሰአት ድረስ አጠቃላይ የመምረጥ መብት ካላቸው ዜጎች መካከል 42.8 እጅ የሚሆነው የመረጠ ሲሆን ፤ ይህም በ2015 ዓ/ም ከተካሄደው ምርጫ አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል።

16:15

 14:47 

የማእከላዊ አስመራጭ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሃናን ሜልጸር ልዩ የሆነ ድርጊት ካልተፈጠረ በስተቀር በምርጫ ጣቢያወች ያለውን ሂደት በካሜራ መቅረጽ እንደማይቻል ከለከሉ። ሜልጸር በድምጽ ቆጠራ ጊዜ መቅረጽ እንደሚቻል ገልጸው የአስመራጩ ኮሚቴ በሚፈቅደው መሰረት በድምጽ ቆጠራው ለተገኙት ሰወች በካሜራ መቀረጹን ማሳወቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ሜልጸር በካሜራ የተቀረጹ ድርጊቶችን ፖሊስ ወይም የማእከላዊ አስመራጭ ኮሚቴ ተወካይ ብቻ ሊመረምር እንደሚችል ውሳኔ አስተላልፈዋል። የማእከላዊ አስመራጭ ኮሜቴው ሊቀመንበር ሜልጸር ይህን ትእዛዝ ያስተላለፉት አረብ እስራኤላዉያን በሚመርጡባቸው ጣቢያወች የሊኩድ ፓርቲ በድብቅ በገጠማቸው ካሜራወችን በተመለከተ  በቀረቡ አቤቱታወች ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።  

  

14:27 

ዛሬ በእስራኤል እየተካሄደ ባለው ብሄራዊ የክነሴት ምርጫ የመምረጥ መብት ካለው ህዝብ መካከል እስካሁን ወጥቶ የመረጠው ህዝብ ከ2015ና ከ2013 የክነሴት ምርጫ ጋር ሲወዳደር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ።

  

12:35

ጠቅላይ ሚንስትር ቢንያሚን ናታንያሁ በየሩሳሌም ከተማ ፖላ ቤንጎሪዮን በተባለው ት/ቤት በተከፈተው ምርጫ ጣቢያ መርጠዋል፡፡ ናታንያሁ በመረጡበት ሰአት በየምርጫ ጣቢያወች ስለተገጠሙት ካሜራወች በሰጡት ሃሳብ ፤  ምርጫውን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ካሜራወች ግልጽ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

ከካሆል ላባን ፓርቲ መሪወች አንዱ የሆኑት ያኢር ላፒድ በቴላቢብ ከተማ በሚኖሩበት አካባቢ ራማት አቢብ በሚገኘው የምርጫ ታቢያ ሂደው መምረጣቸው ታውቋል፡፡

 

 

11፡02

እስራኤል  ዛሬ ብሄራዊ የክነሴት ምርጫ እያካሄደች ነው፤ በመላው እስራኤል 10 ሽህ የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያወች ተከፍተዋል፡፡ ፕረዝዳንት ሩበን ሪብሊን ያፌ ኖፍ በተባለው /ቤት  በተከፈተው የምርጫ ጣቢያ የመረጡ ሲሆን ዜጎች ወደ ምርጫ ጣቢያወች በመሄድ እንዲመርጡ በማሳሰብ የእስራኤል ክነሴት ምን እንደሚመስልና ማን ጠቅላይ ሚንስትር እንደሚሆብን የሚወስ የእስራኤል ዜጎች ናቸው በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የካሆል ላባን ፓርቲ ቤኒ ጋንጽ በሚኖሩበት ሮሽ ሃኢን መርጠዋል፡፡